1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግጭትና ሥጋት

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2011

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ቁጥራቸዉ በዉል ያልተገለፀ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ግቢ ለቀዉ መዉጣታቸዉ ተዘገበ

https://p.dw.com/p/3JT7C
Karte Äthiopien englisch

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርቲ ተማሪዎች ግጭትና ሽሽት


በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ቁጥራቸዉ በዉል ያልተገለፀ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ግቢ ለቀዉ መዉጣታቸዉ ተዘገበ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ በስልክ ያነጋገራቸዉ ተማሪዎች እንዳሉት ግቢዉን ለቀዉ የወጡት አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ናቸዉ።ተማሪዎቹ እንደሚሉት በዩኒቨርስቲዉ ዉስጥ በሳምንቱ ማብቂያ በተፈጠረ የጎሳ ግጭት አንድ ተማሪ ተገድሏል።የዩኒቨርስቲዉ ፕሬዝደንት ግን ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተዉ ተማሪዎችም በከፊል ወደየትምሕርት ገበታቸዉ እየተመለሱ ነዉ።ዝርዝሩን እነሆ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ