1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደብሊኑ ውልና የስደተኞች ዕጣ

ረቡዕ፣ መጋቢት 26 2004

በአውሮፓ ህብረትና በሌሎችም የአውሮፓ ሃገራት አሁን የሚሰራበት የሰደተኞች አቀባበል ደንብ እስካሁን አንድ ማሠሪያ ሳይበጅለት ባለበት የዘለቀ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው ። በተለይ ሰደተኞች መጀመሪያ ከገቡበት ሃገር ውጭ ተገን እንዳይጠይቁ የሚከለክለው አወዛጋቢ

https://p.dw.com/p/14XHC
ምስል picture-alliance/dpa

በአውሮፓ ህብረትና በሌሎችም የአውሮፓ ሃገራት አሁን የሚሰራበት የሰደተኞች አቀባበል ደንብ እስካሁን አንድ ማሠሪያ  ሳይበጅለት ባለበት የዘለቀ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው ። በተለይ ሰደተኞች መጀመሪያ ከገቡበት ሃገር  ውጭ  ተገን እንዳይጠይቁ የሚከለክለው አወዛጋቢ ህግ  በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል  ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ህጉ ያስከተላቸውን ችግሮችና እንዲለወጥ  የሚደረጉ ጥረቶችን ይመለከታል ።

Frankreich Dschungel von Calais Immigranten Demonstration Lebensbedingungen
ምስል AP

ለስደተኞች ከለላ መስጠትን የተመለከተውን የጄኔቫውን ዓለም ዓቀፍ ስምምነትና የአውሮፓ ህብረት  መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ ው  ፣ መጀመሪያ የደብሊን ስምምነት በኋላ ደግሞ 2 ተኛው የደበሊን ደንብ የተባለው  ህግ ዓለም ዓቀፍ ጥበቃ ለሚሹ  ተገን ጠያቂዎች ማመልከዎች ሃላፊነቱን የሚወስደውን አባል ሃገር  ለመወሰን የወጣ ደንብ ነው ። ህጉ ማንኛውም  ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሃገር የሚገባ ስደተኛ ጥገኝነት መጠይቅ የሚችለው መጀመሪያ በገባበት አገር በቻ እንዲሆን  ይደነግጋል ።  በዚህ ደንብ ምክንያት ወደ አውሮፓ የሚመጡ በርካታ ስደተኞች ከገቡባቸው አገራት በግዳጅ እየተባበሩ ነው ። ሶማሊያዊው ስደተኛ ሀሰን ኑር አሊ  አሁን ከጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አቅራቢያ በሚገኝ የሰደተኞች መጠለያ ውስጥ ነው ያለው በአርባዎቹ መጨረሻ  የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ሀሰን አሁን ጀርመን ለመድረስ ብዙ ስቃይ ደረሶበታል ። በሱዳን በኩል ወደ ሊቢያ ከዚያም በሜዲተራኒያን ባህር አድርጎ ከሌሎች 29 ስደተኞች ጋር    በበትንሽ ጀልባ ከሁለት ቀን ጉዞ በኋላ የአውሮፓ ህብረት አባል ወደ ሆነችው ማልታ ደረሰ ። ይሁንና ከስቃይ ያመለጠ ለመሰለው ሃሰን ማልታ የገጠመው ነፃነት ወይም የተሻለ ህይወት ሳይሆን ከወህኒ ጋር የሚስተካከል የሰደተኞች ማጎሪያ ነበር ።

Für projekt Destination Europe Leben im Auffanglager Leben im Auffanglager Verschiedene Wege der Migration
ምስል AP

« ሰኔ 2008 ማልታ ገባሁ ። ከዚያም  1 ዓመት ተኩል እስር ቤት ቆየሁ ። ወንጀለኛ ግን አልነበርኩም ። ሃገሬ ሶማሊያ ትልቅ ችግር ላይ ናት ። በህይወት መቆየት እፈልጋለሁ ። ባለቤቴ ሞታለች ።  3 ልጆቼ ሞተዋል ። ገንዘቤም ቤቴም ወድሟል ። ብቸኛ ነኝ ። »

ሀሰን ሶማሊያ ውስጥ ቤተሰቦቹና እርሱ የአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ሰለባ ከሆኑ በኋላ ነበር ከሃገር የወጣው

።  ክወህኒ በማይተናነሰው የሰደተኞች ማጎሪያ ከአንድ ዓመተ በላይ ማልታቆይቷል ። ሀሰን የማልታ ቆይታውን ሲያስታውስ

«ፖሊስ ውህኒ ቤት አስገባኝ ። በዚያ ቆይታዮ ጤናየ ተቃውሷል ። መድሐኒት አልነበረም ። ምግቡ ጥሩ አልነበረም ። ልብስ የለም ። ፖሊስ አንዳንዴ ይደበድበናል ።ይህን ቅሪታየን ለፖሊስ ስናገር አንድ ለሊት ውጭ ራቁቴን አሳደረውኛል ። »

Demonstration von Asylbewerbern in Belgien
ምስል AP

ህሰን ከአንድ ዓምት በላይ ከቆየበት ማልታ ወደ ኔዘርላንድስ ከተሻገረ በኋላ ወደ ጀርመን መጥቶ የጥገኝነት ማመልከቻ ለማስገባት ሞክሯል  ። ይሁንና  ጀርመን የመቆያ ፈቃዱ ጊዜያዊ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ ወደ ወደ ማልታ ሊላልክ ይችላል ።

« በዚህ ዓመት በጥር ወር አንድ ምሽት ፖሊስ ክፍሌ መጥቶ ዛሪ ማታ በአውሮፕላን ወደ ማልታ ትወሰዳለህ አለኝ ።  ለምን ብዮ ጠየቅኩት ። አላውቅም ማልታ ግን ትሄዳለህ አለኝ ። ማልታ አልሄድም ፤ማልታ ከምሄድ ራሴን አጠፋለሁ አልኩት ። »

ሀሰን ጀርመን መኖር ነው የሚፈልገው ። ይህ ግን ከዛሬ 9 ዓመት በፊት በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን የወጣውን የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበል ህግ ይፃረራል ። በህጉ መሠረት ማንኛውም ስደተኛ መጀመሪያ በገባበት ሃገር ነው የጥገኝነት ማመልከቻ ማስገባት ያለበት ። በዚሁ መሠረት ሃሰን ማመልከት ያለበት ማልታ ነው ።  እንደ ሃሰን ሁሉ ሌሎች ስደተኞችም ተመሳሳይ ታሪክ ነወ ያላቸው ። ሁለተኛው የደብሊን ህግ ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሃገሮች ካለ ፈቃድ የሚገባ ስደተኛ አሻራ በአውሮፓ ደረጃ እንዲያዝ ያደርጋል ። ዓላማው የስደተኛውን ማመልከቻ ተቀባይ ሃገር በፍጥነት ከመለየት በተጨማሪ ተገን ጠያቂውን መቀበል ወደሚገባው ሃገር ማሸጋገርም ነው ። ብዙውን ጊዜ ይህን መሰሉ ሃላፊነት

Hassan Nour Ali
ምስል Aktionsbündnis gegen Dublin II/Lothar Steiner

የሚወድቀው ግን ስደተኛው መጀመሪያ እግሩ በረገጠበት የህብረቱ አባል ሃገር ላይ ነው ። ከሁለተኛው የደብሊን ህግ  በፊት የደብሊን ስምምነት ይቀድማል ።  ስምምነቱን እጎአ ሰኔ 1990 ነበር ደቢሊን አየርላንድ ውስጥ  12 አገራት ማለትም በቤልጂግ ፣ ዴንማርክ ፣ፈረንሳይ ፣ጀርመን ፣ግሪክ ፣አየርላንድ ፣ ኢጣልያ ፣ ላክሰመበርግ  ፣ ኔዘርላንድስ ፖርቱጋል ስፓኝ ና ብሪታኒያ የፈረሙት ። ክዚያም ጥቅምት 1997 ኦስትሪያ ና ስዊድን ከዚያም በጥር 1998 ፊንላንድ ህጉን ተቀብለዋል ። ስምምነቱ የደብሊን ደንብ ተበሎ የፀደቀው ።እጎአ በ 2003 ነው ። ሎታር ሽታይነር ሁለተኛው የደብሊን ህግ የሚቃወም የአንድ ግበረ ሰናይ ድርጅት ባልደረባ ናቸው ።

« ሁለተኛው የደብሊን ደንብ  አውሮፓውያን በሰደተኞች ላይ ለሚፈጥሩት ደንቃራ እንደ ተጨማሪ የግንብ አጥር የሚታይ ነው ። ይህ ደንብ በአውሮፓ የሚገኙ ሰደተኞችን የኑሮ ደረጃ ተሰፋ አስቆራጭ ሁኔታ ላይ የሚጥል  ነው በተለይም  የአውሮፓ ህብረት ዋነኛ አንቀሳቃሳሽ በሚባሉት  በፈረንሳይና በጀርመን ።»

Protest gegen Abschiebepraxis
ምስል picture-alliance/dpa

ከደብሊኑ ደንብ ዋነኛ ዓላማዎች አንዱ ስደተኞች በተለያዩ ሃገራት ተገን መጠየቂያ  ማመልከቻዎችን እንዳያስገቡ መከላከል ነው ። ሌላው ደግሞ ከአንዱ ወደ ሌላው የአወሮፓ ህብረት አባል ሃገር የሚዘዋወሩ ስ

ደተኞችን ቁጥር መግታት ነው ። በህጉ መሠረት ሃላፊነቱ  የሚወድቀው ስደተኛው  መጀመሪያ የገባበት ሃገር ላይ ነው ። እጅግ ብዙ ስደተኞች የሚገቡት ደግሞ የህብረቱ ድንበር በሆኑት ጥቂት አገራት በኩል ነው ። እነዚህ  ሃገራት በሰደተኞች በመጨናነቃቸውም ለተገን ጠያቂዎች  ሲኦል ሆነዋል ።  በፖለቲካ ሳቢያ የሚሰደዱትንና የሌሎችንም ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው የአውሮፓ ምክር ቤት በእንግሊዘኛው ምህፃር ECRE እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር UNHCR አሁን በአውሮፓ የሚሠራበት የሰደተኞች አቀባበል ህግ ለተገን ጠያቂዎች ፍትሃዊ ቀልጣፋና ውጤታማ  ከለላ አይሰጥም ሲሉ ይተቻሉ ። በነርሱ አባባል ደንቡ  የተገን ጠያቂዎችን ህጋዊ መብቶችና የግል ጥቅሞች ይፃረራል ። በአባል ሃገራትም ዘንድ ያልተመጣጠነ የስደተኞች አቀባበል እንዲኖር አድርጓል ። ማመልከቻዎች  መልስ ሳያገኙ እንዲዘገዩና ከማድረጉም በላይ ስደተኞችን የጥገኝነት ማመልከቻ ካስገቡባቸው ሃገራት መጀመሪያ ወደመጡበት ሃገር ለማሻገር  በቁጥጥር ስር ማዋልን ያካትታል ። በዚህ ሂደት ውስጥ የቤተሰብ  መለያየት የሚከሰት ሲሆን ስደተኞችም መጀመሪያ ወደ ገቡበት ሃገር እንዲመለሱ ሲወሰንባቸው ይግባኝ የማለት እድል አይሰጣቸውም ።

Schweiz Einwanderungspolitik Asylbewerber Abschiebung Entwicklungshilfe
ምስል picture-alliance/dpa

በዚህ የተነሳም የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሙሉ በህጉ አይስማሙም ። ህጉ መሻሻል እንደሚገባው የሚያሳስቡ አሉ ። ያም ሆኖ ጀረመን ስደተኞች መጀመሪያ በገቡበት ሃገር ያመልክቱ የሚለውን አቋሟን አልቀየረችም ። ሌሎች አባል ሃገራት ግን ደንቡን የመቀየር ፍላጎት አሳይተዋል ። ሁለተኛው የደብሊን ህግ የህብረቱ ድንበር በሆኑትና ለተገን ጠያቂዎች ድጋፍና ከለላ የመስጠት  አቅማቸው ዝቅተኛ በሆነባቸው ሃገራት ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ነው ። ECRE እና UNHCR የግሪክንየተገንጠያቂዎችን

አያያዝ በይፋበመውቀሳቸውአንዳንድ ሃገራት በደብሊኑ ስምምነት መሠረት ተገን ጠያቂዎችን ወደ ግሪክ  እንዳይላኩ አድርገዋል ።  ኖርዌይ እጎአ በየካቲት 2008  ስደተኞችን ወደ ግሪክ እንደማትመልስ አስታውቃለች ። በሚያዚያ 2008 ደግሞ ፊንላንድ ተመሳሳይ እርምጃ ወሰዳለች ። ጀርመንም እጎአ እስከ 2013 ስደተኞች ወደ ግሪክ እንዳይባረሩ ወሰናለች ። ይሁና ይህ ውሳኔ ሌሎቹን በደቡብ አውሮፓ የሚገኙ እንደ ግሪክ ያሉ ሃገራትን አይጨምርም ። የጀርመን ጥምር መንግሥት ከግሪክ የመጡትን ጉዳይ ብቻ በተለየ ሁኔታ ከማየት በስተቀር ሁለተኛውን የደብሊን ህግ የመለወጥ እቅድ የለውም ።ባለፈው ሳምንት በጉዳዩ ላይ የተነጋገረው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ህጉ እንዲሻሻል መንገዱን አመቻችቷል ። በዚሁ መሠረት ክኮንጎ ከኢራቅ ከቱርክ ከሶሪያ ከሊባኖስ ወይም ከሱዳን የሚመጡ ስደተኞች የጥገኝነት ማመልከቻ የተለይ ትኩረት እንዲስጠው ይደረጋል ። የመብት ተሟጋቾች ስደተኞች በፈለጉበት አገር ጥገኝነት የማመልከት መብት ይሰጣቸው ሲሉ እየተከራከሩ ነው ። የደብሊኑ ህግ ሙሉ በሙሉ ይሰረዝ ባያም ናቸው ።  ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋውር መብታቸው እንዲጠበቅም ይጠይቃሉ ። ሎታር ሽታይነር

«በጀርመንም ሆነ በአጠቃላይ በአውሮፓ ተገን የሚጠይቁ ሰዎች በዚህ ከሚኖሩ ሌሎች ዜጎች በተለየ ሁኔታ ሊታዩ አይገባም ብለን እናስባለን ። ጀርመናውያን ስደተኞች በ1930ና 40ዎቹ ዓመታት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በስደት እንደምሄዳቸው  ሁሉ እዚህም በስደት የሚገቡ ስዎች ነፃ ሆነው ከቦታ ቦታ ነፃ ሆነው መንቀሳቀስና የሚቀመጡበትን ቦታ የመምርጥ እድል እንዲኖራቸው እንፈልጋለን  ። በጀርመን ውስጥ ና በአውሮፓም ሰዎች የመንቀሳቀስ ነፃነት እንዳላቸው ሁሉ እነዚህም ሰዎች ይህ እድል ሊነፈጋቸው አይገባም ።

የመብት ተከራካሪዎች በዚህ አቋማቸው ገፍተዋል ። እንደ ሃሰን ያሉ ስደተኞች እጣ ምን እንደሚሆን ግን አይታወቅም ።

ሂሩት መለሠ

ሸዋዮ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ