የደቡብ አፍሪቃው የስራ ማቆም አድማ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2002ማስታወቂያ
የስራ ማቆም አድማውን የጠሩት የሰራተኛ ማህበራት የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃሚ እስካልሆነ ድረስ የመንግስት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ አስጠንቅቀዋል ። ጥያቄአቸውም 8.6 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን እንዲሁም መንግስት ለመኖሪያ ቤት የሚሰጠው ድጎማ ወደ 1000 የደቡብ አፍሪቃ ራንድ ወይም ወደ 137 ዶላር ከፍ ይደረግልን የሚል ነው ። የደሞዝ ጭማሪውን ከሰባት በመቶ ፈቅ እንደማያደርግ እና ከዚህ በላይ መክፈል እንደማይችል መንግስት አስታውቋል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ