የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ምስረታ መተላለፍ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 10 2008ማስታወቂያ
ከመንግሥት ጋር የተደረሰዉን የሰላም ዉል ተግባራዊ ለማድረግም፣ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚደንትነት ስልጣን ይይዛሉ የተባሉት እና ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው የደቡብ ሱዳን የፓጋክ ከተማ ደርሰዋል የተባሉት የአማጽያን መሪ ማቻር ዛሬ መዲናይቱ ጁባ ገብተው ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ግን ማቻር ጉዟቸውን በ24 ሰዓታት እንዳስተላለፉት ነው የዜና ወኪሎች ያመለከቱት፣ ከብዙ ጊዜ ወዲህ የሚጠበቀው የማቸር ጁባ የመግባት ጉዳይ አሁንም እንደገና ለምን እንደተላለፈ የናይሮቢ ወኪላችንን በስልክ ጠይቀንዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ