የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ስምምነት
ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2006ማስታወቂያ
የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በ60 ቀናት ውስጥ ብሄራዊ የአንድነት የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት መስማማታቸው ተገለፀ ። የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ ዛሬ እንዳስታወቀው የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ውይይት ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል ። ከዚህ በተጨማሪም በግጭቱ ለተጎዳው ህዝብ የሚለገስው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዳይደናቀፍ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል ። የኢጋድ አባል ሃገራት መሪዎች ትናንት በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ማምሻውን ባወጡት መግለጫ መንግሥትና አማፅያን ከዚህ ቀደም የተፈራረሟቸውን ሁለት የተኩስ አቁም ስምምነቶች ባለማክበራቸው ቅር መሰኘታቸውን ሳይገልጹ አላለፉም ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ