የደቡብ ሱዳን ማስተባበያ
ማክሰኞ፣ ጥር 9 2009ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒትየ ሞርጋን አዲስ አበባ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተሰራጨው ዜና ሀሰት ነው ብለዋል። ሱዳን ትሪብዩን የተባለው ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ የሦስቱ ሃገራት መሪዎች፣ በአባይ ወንዝ ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ የምትገነባውን ኢትዮጵያን የሚደግፈውን የሱዳን መንግሥት ለመገልበጥ ለሚታገሉ ታጣቂዎች ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ለመክፈት መስማማታቸውን ተችዎችን ጠቅሶ ዘግቧል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ