1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔ

ዓርብ፣ መስከረም 14 2003

በኒውዮርኩ ስብሰባ 5 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ይካፈላሉ። የደቡብ ሱዳን ህዝበ ውሳኔ ምዕራቡን ዓለም ስጋት ውስጥ ከቷል።

https://p.dw.com/p/PM8m
የደቡብ ሱዳን መሪ ሳልቫኪርምስል AP

በኒዮርክ አምስት የአፍሪቃ አገራት የተሳተፉበት ጉባኤ በደቡብ ሱዳን ህዝበ ዉሳኔ ላይ ስለተፈጠሩ ችግሮች ዛሬ ይወያያል። ከዉይይታቸዉ በተጨማሪም ህዝበ ዉሳኔዉ ወደሌላ ጊዜ እንዳይተላለፍ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ እንደሚሉት በሱዳን ህዝበ ዉሳኔ ላይ ጎረቤት አገራት ያላቸዉ አቋምና ፍላጎት አንድ ችግር ሆኗል። መሠረታዊዉ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ከዚህ ዉሳኔ በኋላ ወደእርስበር ጦርነት ትገባለች የሚለዉ ስጋት ነዉ።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ