የደርባ ስሚንቶ ኢንዱስትሪ መመረቅ
ዓርብ፣ የካቲት 2 2004ማስታወቂያ
በ 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ፤ በሰሜን ሸዋ፤ ደርባ በተባለ አካባቢ የተገነባው የስሚንቶ ኢንዱስትሪ ትናንት በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ተመርቋል። ባለፉት 5 ዓመታት እጅግ በመጨመር በግናባታው ዘርፍ ላይ ብርቱ ተጽእኖ አሳድሮ የነበረውን የሲሚንቶ ዋጋ አዲሱ ኢንዱስትሪ ያረጋጋዋል ፤ በሲሚንቶ ዋጋ መናር ሳቢያ ደከም ብሎ የነበረውን የግንባታ ዘርፍም ያነቃቃዋል ተብሎ እምነት ተጥሎበታል። የኢትዮጵያ ዐመታዊ የስሚንቶ አቅርቦት ከ 600ሺ ቶን አይበልጥም ነበር ፤ ትናንት የተመረቀው ፤ በሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ተገንብቶ በይፋ ሥራ የጀመረው የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ይህንን ምርት በ 2,3 ሚሊዮን ቶን ያሳድገዋል ተብሏል።ከሙገርና ሞሰብ የስሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር የድርባው ኢንዱስትሪ የስሚንቶን ምርት ወደ 9 ሚሊዮን ቶን ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
ታደሰ እንግዳው
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ