አቶ ዮናታን የተላለፈባቸውን ፍርድ እና የተከሰሱበት የወንጀል ጭብጥ ቀለለ።
ሰኞ፣ ኅዳር 18 2010ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ የተላለፈባቸውን ፍርድ እና የተከሰሱበትን የወንጀል ጭብጥ አቀለለ። የአቶ ዮናታንን ይግባኝ የተቀበለው ፍርድ ቤቱ በዛሬው ችሎት ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈባቸውን የ6 ዓመት ከ6 ወር የእሥር ውሳኔ ወደ 3 ዓመት ከ6 ወር ዝቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ሌላ የፀረ ሽብርን ሕግ መሠረት በማድረግ የቀረበባቸውን ክስም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉ ገደቦችን በመተላለፍ በሚል ክስ አቅልሎታል። አቶ ዮናታን የኢትዮጵያን መንግሥት የሚተች ጽሁፍ በፌስቡክ አሰራጭተዋል በሚል ከታኅሳስ 2008 ዓ,ም አንስቶ በእሥር ላይ ናቸው። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ጠበቃቸውን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ