የዩክሬይን ውዝግብ፣ ሩስያ እና ምዕራቡ ዓለም
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2006ማስታወቂያ
ለሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ቅርበት አላቸው በተባሉ ሰባት የሩስያ ባለሥልጣናት እና 17 ኩባንያዎች ላይ ነው። ማዕቀቡ በተጨማሪ ለሩስያ የጦር ኃይል አስፈላጊ የሆኑ ከውጭ የሚገቡ ከፍተኛ የቴክኒክ ቁሳቁሶችንም የሚመለከት ነው። ከአሜሪካውያኑ ጋ ሲነፃፀር የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ በግለሰቦች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው። ህብረቱ እንደ ዩኤስ አሜሪካ የሩስያን ኤኮኖሚ ወይም ፊናንስ ዘርፍ የሚነካ ጠንካራ ማዕቀብ እስከመጣል ግን ርቆ አልሄደም፣ ምክንያቱ ምን ይሆን? የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ቀደም ሲል ጠይቄው ነበር።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ