1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ አሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሶርያ ጉብኝት

ረቡዕ፣ መጋቢት 26 1999

የዩኤስ አሜሪካ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ናንሲ ፔሎዚ ዛሬ በደማስቆ ከፕሬዚደንት በሺር ኤል አሳድ ጋር ተገናኝተው ሀሳብ ተለዋወጡ። -------> ይዞራል

https://p.dw.com/p/E880
ናንሲ ፔሎዚ እና ፕሬዚደንት አሳድ
ናንሲ ፔሎዚ እና ፕሬዚደንት አሳድምስል AP
ትናንት ከሶርያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋሊድ አል ሞላምና ከምክትል ፕሬዚደንት ፋሩክ ኤል ሻራ ጋር የተወያዩት ፔሎዚ የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት ሽብርተኝነትን ታስፋፋለች የሚላትን ሶርያ በመጎብኘታቸው ብርቱ ነቀፌታ ሰንዝሮባቸዋል። አንድ ከፍተኛ የዩኤስ አሜሪካ ፖለቲከኛ ከብዙ ዓመታት ወዲህ ለውይይት ወደ ሶርያ ሲጓዙ ፔሎዚ የመጀመሪያዋ ናቸው።