የዩኔስኮ ዓመታዊ ዘገባ
ረቡዕ፣ ጥር 21 2006ማስታወቂያ
ድርጅቱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ዘገባ እንዳስታወቀው ቁጥራቸው ወደ ሩብ ቢሊዮን የሚጠጋ ሕፃናት አንድን አረፍተ ነገር ጠንቅቀው ማንበብ አይችሉም ፤ ተገቢውን የሂሳብ ትምህርትም አያገኙም ። በአፍሪቃ በብዙ ሚሊዮን ለሚቀጠሩ ወጣቶች መሠረታዊ ትምህርት አለመዳረሱም አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ አዲስ አበባ ውስጥ አስታውቋል ። በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ቢኖርም የጥራት ችግር እንዳልተወገደ ድርጅቱ አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ