የንግድ ዉዝግብ
ዓርብ፣ የካቲት 30 2010ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ከዉጪ በምታስገባቸዉ የብረትና የአልሙኒንየም ማዕድናት ላይ ተቸማሪ ግብር መጣልዋ ከረጅም ጊዜ የንግድ ተሻራኪዎችዋ ጋር እያወዛገባት ነዉ።የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር እንዳስታወቀዉ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የብረት እና የአልሙኒየም ማዕድናት ላይ የ25 ከመቶ እና የ10 ከመቶ ጭማሪ ግብር ጥሏል።የዩናይትድ ስቴትስን እርምጃ የተለያዩ ሐገራት ሲቃወሙት ቻይና እና የአዉሮጳ ሕብረት አፀፋ እርምጃ ለመዉሰድ እየዛቱ ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ