የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ጉባኤ ፍጻሜ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 1 2006ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰላም አሰከባሪ ኃይል ማቋቋሚያ 110 ሚሊዮን ዶላር ለመመደብ ማቀዷን አስታወቀች ።ትናንት በተጠናቀቀው የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው ሃገራቱ ደፈጣ ተዋጊዎችንና ሌሎች ችግሮችን እንዲቋቋሙ እገዛ ያደርጋል የተባለውን ይህንኑ ኃይል ለመመስረት የሚውለውን ገንዘብ ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው በሚቀጥሉት ሶሶት ዓመታት ነው ።በዚሁ ፈጥኖ ደራሽ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት የአፍሪቃ አገራት ይካተታሉ ።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ ለሦስት ቀናት በተካሄደው በዚሁ ጉባኤ ፍፃሜ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው በንግድ በመልካም አስተዳደርና በደህንነት ጉዳዮች ላይ ተጨባጭ እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።
አበበ ፈለቀ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ