የዩኒቨርስቲ ምሩቃንና የሚጠብቋቸው ሥራዎች
ዓርብ፣ ሐምሌ 6 2004ማስታወቂያ
ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ ከሚባሉ መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ ነው። ያም በመሆኑ ሀገራት በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ገንዘብ ሲያፈሱ እና የሰው ሀይል ሲያሰማሩ ይታያል። በኢትዮጵያም የሀገሪቱ አንጡራ ሀብት የፈሰሰባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በየጊዜው ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ይወጣሉ፤ በየተመረቁበት የትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው ሀገራቸውን ለማገልገል በማሰብ። ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቁ ተማሪዎች ዲግሪ ይዘው በድንጋይ ጠረባ ይሰማራሉ የተባለለትን የሰሞኑ የመነጋገሪያ ርዕስ ይዘን ተመራቂ ተማሪዎችን አነጋግረናል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ