የዩኒሴፍ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት በእናቶች እና በህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እና የእናቶች እና ህፃናትን ጤና ለማስጠበቅ ከዩኒሴፍ ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የመግባባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ።ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች በእምነቶቻቸው መሠረት ፣በእናቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሃይማኖታዊ ተቀባይነት የላቸውም ብለዋል ።ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ