የዩሊኽ የምርምር ማዕከልና ፣ በአውሮፓ እጅግ ግዙፉ ኮምፑዩተር፣
ረቡዕ፣ የካቲት 18 2001ማስታወቂያ
በውቅያኖስ የሚገኙ እንስሳትና ዐራዊት ፣ የተለያዩ ነፍሳት በተለያዩ ደኖች የሚገኙ ዕጽዋትና ነፍሳት ፣ የምድር ነውጥ ፣ እሳተ-ገሞራዎች ፣ እነዚህና የመሳሰሉት የተሟላ ምርምር ተደርጎባቸዋል ማለት አይቻልም።
ለምርምር ሰፊ እገዛ የሚያደረጉ የሥነ- ቴክኒክ ውጤቶች መሆናቸው የማይታበል ሐቅ ነው። በመሆኑም ለዚህ የረጅም ጊዜ ግንዛቤ ያላት ጀርመን፣ በአውሮፓ እጅግ ግዙፉን የስሌት ኮምፑዩተር ኮሎኝ አቅራቢያ ዩሊኽ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ታዋቂ የምርምር ማዕከል እንደምትተክል አስታውቃለች።