የዘጋቢ ፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ሰኔ 5 2007ማስታወቂያ
ኢኒሽየቲቭ አፍሪቃ አዲስ ኢንተርናሽናል የተባለው የፊልም ፌስቲቫል ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ ለአምስት ቀናት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ይካሄዳል።በዚሁ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ዝና ያተሩፉ 50 ምርጥ ዘጋቢ ፊልሞች እንደሚቀርቡ አዘጋጆች ተናግረዋል ። ዘጋቢ ፊልሞቹ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ናቸው ።የፊልም ፊስቲቫሉ በአዲስ አበባ በቅርስ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በሃገር ፍቅር፣ በብሪቲሽ ካውንስልና በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ እንዲሁም በናዝሬት ፣በመቀሌ፣ በድሬዳዋና በአዋሳም ይካሄዳል ። አዘጋጆቹ ስለ ፌስቲቫሉ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ