የዘንድሮው ሃጂና ኢትዮጵያውያን ተጓዞች
ዓርብ፣ ጥቅምት 16 2005ማስታወቂያ
ሙስሊም ምዕመናን በየአመቱ እንደሚያደርጉት ዘንድሮም ለሃጂ ሳውዲ አርቢያ መካ ና መዲና ይገኛሉ። ለዚሁ ሃይማኖታዊ ጉዞ ከ 198 ሃገራት የተሰባሰቡ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ሃጃጆች ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሳውዲ ሃጅና ኡመራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ ይጠቁማል። ቁጥራቸው ከ 6 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንም የዚሁ ሃይማኖታዊ ጉዞ ተካፋይ ናቸው። የዘንድሮው ጉዞና መስተንግዶ እንዴት እንደነበር የጂዳው ወኪላችን ነበዩ ሲራክ ኢትዮጵያውያኑን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ