የዘር ፖለቲካ እንዲታገድ የጠየቀ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ በዋሽንግተን ዲሲ የመጀመሪያው የኾነው የተቃውሞ ሰልፍ ትናንት ጠዋት ተደርጓል። የሰልፉ ዓላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዘር ፖለቲካ የሚቃወም እና ይታገድ የሚል ነው። ሰልፉ የተከናወነው ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ነበር። ከሰልፉ በኋላ የሰልፉ አስተባባሪዎች ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ደብዳቤ አስገብተዋል። ዝርዝር ዘገባውን መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ።
መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ