የዓለም የፕረስ ሽልማት ለኢትዮጵያዊዉ ጋዜጠኛ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005ማስታወቂያ
ጋዜጠኛ መሥፍን ነጋሽና ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ታሥረው ለተፈቱት 2 የእስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢዬና ዮሐን ፔርሶን ፤ እ ጎ አ የ 2013 የዓለምን የፕረስ ሽልማት ሰጥቷል። 3 ቱ ጋዜጠኞች ይህ ሽልማት የተሰጣቸው፤ ሐሳብን በነጻ መግለጽና ጋዜጠኝነት በአሸባሪነት በሚያስወነጅልባት ሀገር የጋዜጠኝነትን ኀላፊነት ለመወጣት ላደረጉት ጥረትና ላሳዩት ጽናት መሆኑም ተገልጾአል። ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽን አዜብ ታደሰ በስልክ አግኝታ አነጋግራዉ ነበር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ