የዓለም የጦር መሣሪያ ዝውውር
ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2008ማስታወቂያ
በዓለማችን ከጎርጎሮሳዊው 2011 እስከ 2015 ከተሰራጨው የጦር መሣሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የሚያመርቱና የሚያሰራጩ ዩናይትድ ስቴትስና ሩስያ መሆናቸው ተዘገበ ። የስቶክሆልም ዓለም ዓቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም በምህፃሩ «ሲፕሪ» ትናንት 50 ኛ ዓመቱን ሲያከብር ይፋ ባደረገው የጦር መሣሪያ ዝውውር መዘርዝር መሠረት በዚህ ጊዜ ውስጥ በጦር መሣሪያ ንግድ የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዘው ዩናይትድ ስቴትስ ለ96 ሃገራት የጦር መሣሪያዎችን ሸጣለች ። ከዩናይትድ ስቴትስ የጦር መሣሪያ በመሸመት ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ሳውዲ አረቢያ ስትሆን የተባበሩት አረብ ኤምሪቶችና ቱርክም ሁለተኛ ና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።የምዕራብ አውሮፓ ሃገራትም በጦር መሣሪያ ሽያጭ ከፍተኛ ቦታ ይይዛሉ ። የስቶክሆልሙ ወኪላችን በ SPRI 50 ኛ ዓመት በዓል አከባበር ተገኝቶዋል።
ቴድሮስ ምህረቱ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ