የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፕዮና
ዓርብ፣ የካቲት 30 2004ማስታወቂያ
14ተኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፕዮና ዛሬ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ ተጀምሯል ። በ የ 2 ዓመቱ አንዴ በሚካሄደው በዚህ ውድድር አትሌት መሠረት ደፋርን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ተካፋይ ናቸው ። ዛሬ ጠዋት በ 3 ሺህ በ 1500 እና 800 ሜትር ሩጫ የማጣሪያ ውድድሮች ተደርገዋል ። በነዚህ ማጣሪያዎች የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማለፋቸውን ከኢስታንቡል ቱርክ ያነጋገርኳት ጋዜጠኛ ሃይማኖት ጥሩነህ ተናግራለች ። ስለ ውድድሩ አጀማመርና ስለ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይዞታ ከሃይማኖት ጋር የተደደረገው ቃለ ምልልስ እነሆ