የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባኤ በሮም
ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2003ማስታወቂያ
ከትናንት በሰተያ ሰኞ ተጀምሮ አርብ የሚያበቃው ይኽው ጉባኤ በተለይ በምግብ ዋጋ ንረትና በ መሬት ሽምያ ምክንያት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው የምግብ ዋስትና ሁኔታ ይመረምራል ። የዓለም የምግብ ና የእርሻ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር FAO ሩስያ ስንዴን የመሳሰሉ ምርቶች ለውጭ ገበያ እንዳይቀርብ በማገዷ የምግብ ዋጋ ቢንርም ዘንድሮ በዓለም ዙሪያ የተሻለ ምርት ስለተገኘ እጎአ በ2007 - 2008 የደረሰው ዓይነት የምግብ ዕጥረት ያጋጥማል የሚል ስጋት ሊኖር እንደማይችል በቅርቡ አስታውቋል ። ይሁንና ፋኦና ሌሎች ሮም የሚገኙ የምግብ ድርጅቶች የምግብ ዋስትና አሁንም አስተማማኝ አይደለም ሲሉ ማሳሰብ ላይ ናቸው ።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ፣ ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ