የዓለም የምግብ ዋስትና መዘርዝርና ኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2004የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ዴታ አስታውቀዋል ። ሚኒስትር ዴታ ምትኩ ካሳ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት አሰራሮች አንዱ የ Safety net ወይምየምግብለሥራመርሃግብርነው።ያምሆኖኢትዮጵያበጥር2004 ይፋእንዳደረገችውከህዝብዋ3.2 ሚሊዮኑየምግብእርዳታጠባቂ ናቸው
ትናንትይፋበሆነውየዓለምየምግብዋስትናመዘርዝርመሰረትከሰሃራበስተደቡብያሉየ 4 የአፍሪቃሃገራትየምግብዋስትናከዓለምበዝቅተኛደረጃላይይገኛል።እነርሱምኢትዮጵያሩዋንዳናይጀሪያናሞዛምቢክናቸው።ኢትዮጵያ ጥናቱ ከተካሄደባቸው 105 አገሮች በምግብ ዋስትና 100 ኛ ደረጃ ነው የተሰጣት ። በመዘርዝሩ ኢትዮጵያ ያገኘችውን ደረጃ መነሻ በማድረግ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ዴታ አቶ ምትኩ ካሳ በሰጡት አስተያየት የሃገሪቱ የምግብ ዋስትና ዝቅተኛ መሆኑ እንደሚታወቅ ገልፀው ሆኖም ሃገሪቱ ባወጣቻቸው እቅዶች መሰረት ውጤቶች መገኘታቸውን አብራርተዋል።
ምንም እንኳን በምግብ ለሥራ መርሃ ግብር ታቅፈውየነበሩ ወደ 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ ዋስትና ተረጋግጧል ቢባልም ፤ ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ዘንድሮም የምግብ እርዳታ ተቀባይ ናቸው ።በአብዛኛው በዝናብ ላይ ጥገኛ በሆነው የኢትዮጵያ ግብርና በዓመት ውስጥ የሚጥለው ዝናብ በአጠቃላዩ ምርት መጠንና በምግብ ዋስትና ላይም ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ። ዘንድሮ እንደ ሶማሊያ ባሉ ጎረቤት ሃገራት የዝናብ እጥረት የምግብ ችግር አሰከትሏል ። ኢትዮጵያስ ይህ ያሰጋት ይሆን ? አቶ ምትኩ
ዋናጽህፈትቤቶቹለንደንኒውዮርክናሆንኮግየሚገኙትEconomist Intelegence Unit የተባለውየምጣኔሃብትአጥኚቡድንየዓለም የምግብ ዋስትና መዘርዝሩንለማውጣትየተጠቀመባቸውመመዘኛዎችበየአገሮቹምግብየመግዛትአቅም፣የምግብመገኘትእንዲሁምየምግብጥራትናደህንነትናቸው።በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየናረ የሄደው የምግብ ዋጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑ ይነገራል ። ይህም በሃገሪቱ የምግብ ዋስትና ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ እንደማይቀር ይገመታል ። ሚኒስትር ዴታ ምትኩ ካሳ ግን ችግሮቹ ጊዜያዊ ናቸው ይላሉ ።
ሒሩት መለሠ
ሸዋዬ ለገሠ