የዓለም ዓቀፍ ግጭት ጥናት ተቋም ዘገባና ኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ መስከረም 7 2002ማስታወቂያ
በኢትዮጲያ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በአግባቡ ስራ ላይ ካልዋለ በአገሪቱ የሚታየዉ የፖለቲካ ዉጥረትና ጫና ተባብሶ ያልተፈለገ መስመር ዉስጥ እንዳይገባ ያሰጋል ሲል ዓለም ዓቀፉ የቀዉስ ፈቺ ተቋም ICG ዘገባ ይፋ አድርጓል። ICG አያይዞም በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ በአገሪቱ አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ለመዘርጋት የወሰደዉ ርምጃ አዳዲስ ዉጥረቶችን ማንገሱን ጠቁሟል።
ሸዋዬ ለገሠ፣
ተክሌ የኋላ፣