የውስጥ አካላትን አጎልቶ የሚያሳየው ግዙፍና የረቀቀ መሣሪያ፣
ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001ማስታወቂያ
በአውሮፓ ወደር እንደሌለው ከተነገረለት ግዙፍ ኮምፒዩተር ሌላ፣ ለህክምና ሥነ-ቴክኒክ እጅግ ጠቃሚ የሆነ፣የሰውነት የውስጥ አካላትን ም ሆነ ኅዋሳትን እጅግ አጉልቶ በማሳየት ይበል ያሰኘ ግዙፍና ረቂቅ መሣሪያ ተሠርቷል። 1,500 እስኩየር ሜትር ስፋት ባለው ቦታ በተሠራ ህንጻ ውስጥ የሚገኘው በመግነጢሳዊ ኃይል የሚሠራው መሣሪያ ፣«ቶሞግራፍ»፣ 4 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ የማግኔቱ ክብደት 57 ቶን ነው። እንደ ምድራችን የተፈጥሮ መግነጢሳዊ ኃይል፣ 190,000 እጥፍ ጉልበትም ያለው ነው።
ተክሌ የኋላ/አርያም ተክሌ