የወጣቶች ግጭት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 11 2012ማስታወቂያ
ሰኞ መስከረም 10/ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የወጣቶች ግጭት የተወሰኑት ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ሲገቡ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱት ለእስር መዳረጋቸውን ዶቼ ቬለ / DW /ያነጋገራቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ቀለም ያለውና ከጀርባው የምኒልክ ምስል የታተመበትን ቲሸርት "ለምን ለበስሽ? " ፤ " ብለብስስ " በሚል የተጀመረ ነው ያሉት የአይን እማኞች ሁኔታው ከአካባቢው ፖሊስ አቅም በላይ ሆኖ በርከት ያሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከደረሱ በኋላ ሊበርድ መቻሉንም ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ወደ 2 መቶ የሚደርሱ ወጣቶች ታስረው እንደነበርና አብዛኞቹ ቢፈቱም ወደ 50 ያህሉ አሁንም አለመፈታታቸውንም አስታውቀዋል። ችግረል በተከሰትልበት ክፍለ ከተማና የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ጣቢያ ተገኝተን እንደተመለከትነው ፣ ወጣቶች ታስረዋል ጠያቂዎችም ያለ እረፍት ወደ ጣቢያው ሲገቡና ሲወጡ ተመልክተናል። ጥፋቱን አደረሱ የተባሉትን ወጣቶች እንዲሁም የከተማዋን ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ሊሳካ አልቻለም ።
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ተስፋለም ወልደየስ