የወጣት ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር
ዓርብ፣ ግንቦት 15 2006ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር ከተቋቋመ በኃላ፤ በአዲስ አበባም ሆነ በክፍለ ሀገር የሚገኙ በርካታ ወጣት ሰዓልያን እና ቀራፅያን ልምድ መለዋወጥ መጀመራቸዉ ተነግሮአል። ስለ ሥነ-ጥበባቱ ማህበር እንቅስቃሴ የለቱ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።
የዛሬ ሶስት ዓመት አዲስ አበባ ላይ የተቋቋመዉ ሰዓልያን እና የቀራፅያን ማኅበር፤ በተለይ በርካታ ወጣት የስነ-ጥበብ ሰዎችን ማሰባሰቡ ተነግሮለታል። የማኅበሩ ዋና ፀኃፊ ወጣት ሰዓሊ ሰይፉ አበበ፤ ሰዓሊያን እና ቀራፂያን በማኅበር ባለመሰባሰባቸዉና ልምድ ባለመለዋወጣቸዉ ይህ ማኅበር ሊቋቋም ቻለ ሲል ገልፆልናል።
የሰዓልያን እና የቀራፅያን ማህበሩ ከተቋቋመ በኃላ በዚህ ሶስት ዓመት ዉስጥ በየዓመቱ የሚዘጋጅ አዉደ ርዕይ እንደሚኖርና፤ እስከ ዛሪም በተደረጉ አነስተኛ ዓዉደ-ርዕዮች በርካታ የሥነ-ጥበብ ሥራዎች መሸጥ መቻሉና ወጣቱ የስነ-ጥበብ ፍላጎቱን የሚያሟላበት ቁሳቁስ መግዣ ሟሟያ ሊያገኝ የሚችልበት መንገድ መፈጠሩን ወጣት ሰይፉ ተናግሮአል። ማኅበሩ ሥነ- ጥበብን ለህዝብ ከማስተዋወቅ እና ሰዓሊዉ የሚጠቀምበትን ከማመቻቸት ባሻገር፤ ልምድ መለዋወጫ የዉይይት መድረክ እንዳለም ይገልፃል። ከአንድ ሳምንት በኃላ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዓመታዊ የሥነ-ጥበብ ፊስቲቫል፤ ለማዘጋጀት በሥራ ተጠምዶ እንደሚገኝ የማኅበሩ ዋና ፀኃፊ ወጣት ሰዓሊ ሰይፉ አበበ ገልፆአል። ሰዓሊ ሰይፉ በሥነ-ጥበቡ ረገድ ባለፉት ዓመታት በርካታ ወጣቶች ከፍተኛ ፍላጎትና ድንቅ ሥራ እያሳዩ መምጣታቸዉን ገልፆአል።
የዛሪ ሶስት ዓመት ሶስት ወጣት ሰዓሊዎች እና ቀራፅያን ተሰባስበዉ ያቋቋሙት ጥላ ማኅበር ቢኖሩም በአሁኑ የኑሮ አያያዝ የሁሉን ጥረት እንደሚጠይቅ የማኅበሩ ፀሐፊ ሳይገልፅ አላላፈም።
ወጣት የሰዓልያን እና የቀራፅያን ማኅበርአዲስ አበባ በሚያዘጋጀዉ ፊስቲቫል ላይ የሥነ-ጥበብ አፍቃሬዎች ተገኝተዉ አስተያየት እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪዉን አቅርቦአል። ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ መጫዉን በመጫን ያድምጡ።
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ