የወባ በሽታ አሳሰቢነት በደቡብ ክልል
ማክሰኞ፣ መስከረም 6 2012ማስታወቂያ
የወባ በሽታ አሳሰቢ ከሆነባቸው አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ክልል ነው። የክልሉ ጤና ቢሮ እንደሚለው ካለፈው ዓመት አጋማሽ አንስቶ የበሽታው ሥርጭት ጨምሯል።ሀዋሳ ወደ ሚገኘው የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሚመጡት ህሙማን አብዛኛዎቹ በወባ የተያዙ ናቸው።የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ክልሉ የተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎችን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ይናገራል።በክልሉ የወባ ሥርጭት የሚገኝበት ደረጃ ፣የሥርጭቱ ምክንያት እና ሥርጭቱን ለመግታት የሚደረጉ ጥረቶች የዛሬው ጤና አካባቢ ዝግጅታችን ትኩረት ነው።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሠ