የወሊድ መከላከያ ለወንዶች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 14 2001ማስታወቂያ
ወንዶችም በዚህ የጋራ ኃላፊነት እንዲሳተፉ የሚያደርግ ግኝት ብቅ ብሏል። የወንዶች የወሊድ መከላከያ መድሃኒት። ይህ መድሃኒት በተለያየ መልኩ ነዉ የቀረበዉ። በመርፌ፤ ቆዳ ላይ በሚቀባ ክሬምና በሰዉነት ዉስጥ በሚቀበር መልኩ። ምርምሩ ዉጤታማነቱ እስካሁን በ400 ጥንድ ባልና ሚስቶች ላይ ተሞክሯል። እዚህ ጀርመን በሙንስተር ከተማ ብቻም ሃምሳ ጥንዶች ሞክረዉታል። እንደታሰበ ምርምሩ ከዘለቀና የመድሃኒት ፋብሪካዎች ሊያመርቱት አቅሙ ካላቸዉ ቢያንስ በአዉሮፓዉያኑ 2012ዓ,ም ገበያ ላይ ይዉላል ተብሎ ይጠበቃል።
ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ