1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ወረርሺኝ በአዉሮጳ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 14 2013

አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ መጠኑን እየለዋወጠ፣ ወረርሺኙን ለመከላከል በየሐገሩ የሚወሰደዉ እርምጃም ጠንከርና ላላ እያለ እንደቀጠለ ነዉ።የወረርሺኙ መከላከያ ክትባት  በተፈለገዉ ፍጥነት ለሕዝቡ አልተዳረሰም

https://p.dw.com/p/3r08Q
EU Ursula von der Leyen PK zu COVID-19
ምስል John Thys/AFP/REUTERS

አዉሮጳና ጀርመን-የኮሮና ስርጭትና መከላከያዉ በአዉሮጳ

                                

አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ መጠኑን እየለዋወጠ፣ ወረርሺኙን ለመከላከል በየሐገሩ የሚወሰደዉ እርምጃም ጠንከርና ላላ እያለ እንደቀጠለ ነዉ።የወረርሺኙ መከላከያ ክትባት  በተፈለገዉ ፍጥነት ለሕዝቡ አልተዳረሰም።የክትባቱ አሰጣጥ አዝጋሚነት የአዉሮጳ ሕብረትን ለጠንካራ ትችት አጋልጦታል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት እዚህ ብራስልስ ባደረጉት ስብሰባ በተለያዩ  አገሮች የሰባዊ መብት ጥሰትን ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ ባሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የማዕቀብ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ማዕቀቡ የጉዞ ዕገዳ የሚያደርግና  የንብረት ማንቀሳቀስን የሚከለክል ሲሆን፣ ውሳኔ የተላለፈባቸውም ከቻይና ስሜን ኮሪያ፣ ሊቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢርትራና ሩሲያ የተመረጡ አስራ አንድ ግልሰቦችና አራት ተቋማት መሆናቸው ተገልጿል። 

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው በሰባዊ መብት ጥሰቶች ላይ ትኩረት ያደረገ  መሆኑን ገልጸዋል፣ `እርምጃው ኢላማ ያደረገው የትም ይሁን  የት ግን ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ላይ ነው። ሁሉም የአውሮፓ  ህብረት የማዕቀብ እርምጃዎች የዓለማቀፍ ህግን ተከትለው ተግባራዊ ይሆናሉ` በማለትም አፈጻጸማቸው አብራርተዋል።

Weltspiegel 19.03.2021 | Corona | Impfstoff AstraZeneca, Europa
ምስል Alexandre Marchi/Photopqr/L'Est Républicain/picture alliance

 የማዕቀቡ እርምጃ ከተወሰደባቸው አራቱ ግለሰቦች፣  በቻይና ዚንጂያንግ ግዛት በሙስሊሞች ላይ በሚፈጸሙ ከፍተኛ  የሰብዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። አሜርካ ብርታኒያና ካናዳ በቻይና ላይ ተመሳሳይ  የማእቀብ እርማጃዎችን በመውሰድ፣ የአውሮፓ ህብረትን እንደተቀላቀሉ የታወቀ ሲሆን፣ እ እ እ በ1989  ዓም በቲአናንመን  አደባባይ ግድያ ምክኒያት ህብረቱ አሳልፎት ከነበረው ማዕቀብ ወዲህ፣  የአውሮፓ ህብረት በቻያና የማዕቀብ ውስኔ ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል

 ቻይና ህብረቱ ያሳለፈውን የማዕቀብ ውሳኔ ተከትሎ፣ በ10 አውሮፓውያን ግለስቦችና ተቋማት ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች መሆኑን አስታውቃለች። ሚስተር ቦርየል ይህ የቻይና እርምጃ፣ ህብረቱ እየወሰዳቸው ካሉት ህጋዊ እርምጃዎች አያስቆመውም በማለት.፣ ቻይና እንደዚህ አይነት የአጸፋ እርምጃዎች ውስጥ ከምትገባ፣ ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ አቅርበዋል።   

የማዕቀቡ እርምጃ ኢላማ ካደረጋቸው ሶስት የአፍርካ አገሮች አንዷ  በሆነችው ኤርትራ ላይ ማቀቡ የተጣለው፣ በሚፈጸሙ የሰባዊ መብት  ጥሰቶች፣ ግድያዎችና የሰዎች መሰወር ወንጀሎች  ምክኒያት መሆኑ ተገልጿል። ማዕቀቡ ኢላማ ያደረገውም በተለይ የኢርትራ  ብሄራዊ ደህንነት ቢሮና ሀላፊው ጀነራል አብርሀ ካሳ ላይ ነው። በውሳኔው ላይ የኢርትራን መንግስት አስተያየት ለማካተት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ግን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን፣ `በኢርትራ መንግስትና ህዝብ ላይ ያነጣጠረና መሰረት በሌለው ክስ ላይ የተመሰረተ` ሲል  አጣጥሎታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ  በኢትዮጵያ ላይም የተወያዩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ህላፊው በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ችግር ወዲህ በየእለቱ በርካታ የሰባዊ መብት ጥሰት ዘገባዎች የሚደርሷቸው መሆኑን የገለጹት ሚስተር ቦሪየል፣ ይህ ሁኒታ መቀጠል የሌለበት በመሆኑ አሁንም ግፊታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።` `የስባዊ እርዳታ ያለገደብ በሁሉም ቦት እንዶደርስ፣  የተፈጸሙ ሰባዊ መብት ጥሰቶች  በገለልተኛ ቡድን እንዲጣሩና የኤርትራ  ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ግፊታችንን እንቀጥላለን በማለት በሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቄ በሆኑ ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች እያጤኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። ሀላፊው አክለውም የፊንላድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር  ሚስተር ፔካ ሃቪስቶ ለተመሳሳይ ተለእኮ በድጋሜ ወደ ኢትዮጵያ የሚሂዱ መሆኑንም ገልጸዋል።

Weltspiegel 19.03.2021 | Corona | Frankreich Paris, Patient
ምስል Christophe Archambault/AFP/Getty Images

በሌላ በኩል ሚስተር ሃቪስቶ በአንድ ፖሎቲኮስ በተሰኘ ጋዜጣ በሰጡት ስተያየት፣ በኢትያጵያ ሰሜናዊ ክፍል ባለው ሁኒታ  ሶስት መሰርታዊ ችግሮችና ያዩ መሆኑን አውስተው፤ እነሱም የሰብዊ እርዳታ ጉዳይ፣ የሰባዊ መብት ጥሰቶችና የጦርነቱ መቆምና የሰላም መከበር ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል ። በሁለቱ ማለት የሰባዊ እርዳታ መድረስና የሰባዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ላይ፣  አንዳንድ መሻሻሎች እየታዩ ቤሆንም፣ በሶስተኛውና በማዕከላዊው መንግስትና የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ውይይት እንዲያካሂዱ የማድረጉ  ጉዳይ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ አስታውቀዋል:፣ መንግስት አማጽያኑ መሳሪያቸውን አውርደው እጃቸውነ እንዲሰጡ እየጠየቀ ቢሆንም፣ ይህ ግን በቀላሉ እውን ይሆናል ብለው እንደማይምኑና ለተሻለ ውጤትም የአውሮፓ ህብረት ከአሜርካ ጋር በህብረት ቢሰራ ጥሩ እንደሚሆን ለጋዜጣው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። 

 

የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅት አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርኝ ያደረሰዉን ጉዳትና ወረርሺኙን ለመከላከል የአዉሮጳ ሕብረት የሚያደርገዉን ጥረት ይቃኛል።

 ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ