1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ፖሊስ 23 ኢትዮጵያዉያንን ከጥቃት አዳነ

ሐሙስ፣ መጋቢት 1 2008

የኬንያ ፖሊስ በተቆጡ ኬንያዉያን የተከበቡ 23 ኢትዮጵያዉያንን ከኃይል ጥቃት ማዳኑ ተዘገበ። በአንድ የተፋፈገ መኖርያ ቤት ተደብቀዉ የተገኙት ኢትዮጵያዉያን ባሉበት አካባቢ ወንጀል መፈፀሙ ካስቆጣቸዉ ኬንያዉያን ዓይን ዉስጥ የገቡት በድንገት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1IAaC
Kenia Attentat in Garissa
ምስል picture-alliance/AP Photo

[No title]

ፖሊስ እነዚህን ኢትዮጵያዉያን ሕገ-ወጥ ስደተኞች ያዳነዉ ልዩ የመከላከያ ኃይል ጠርቶና ወደ ሰማይ ተኩሶ መሆኑ ተመልክቶአል። በአሁኑ ወቅት እስር ቤት እንደሚገኙ የተነገረዉ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን አብዛኞቹ ምንም ዓይነት መታወቂያ የሌላቸዉ ናቸዉ። ኪስዋሂሊም ሆነ እንጊሊዘኛ ቋንቋ አለመናገራቸዉ ነገሩ ን እንዳከበደባቸዉም ፖሊስ ተናግሮአል። ስለ ሁኔታዉ ኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይቄዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ