የኬንያ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ያሳለፈው ብይን
ሰኞ፣ መስከረም 17 2003ማስታወቂያ
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሚንገላቱባቸው አገራት አንዷ ኬንያ ናት ። በኬንያ የተለያዩ አካባቢዎች የስደት ኑሮ የሚገፉ ኢትዮጵያውያን በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለእስር እና ለወከባ እንደሚዳረጉ በየጊዜው የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ ። በቅርቡ ደግሞ ሰማንያ ዘጠኝ የሚሆኑ ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲባረሩ በፍርድቤት ተወስኖባቸዋል ። ። በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ስለተላለፈው ስለዚሁ ብይን መሳይ መኮንን አንድ ኬንያዊ ጋዜጠኛ እና አንድ ኬንያ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።
መሳይ መኮንን
አርያም ተክሌ