የኬንያ ጊዚያዊ ሁኔታ
ሰኞ፣ ነሐሴ 8 2009ማስታወቂያ
የኬንያ የምርጫ እና የድንበር ኮሚሽን የኦዲንጋን ወቀሳ አጣርቶ ምርጫው አልተጭበረበረም ቢልም እና ዓለም አቀፍ ታዛቢ ቡድኖች ምርጫው ነጻና ትክክለኛ እንደነበር ቢያመለክቱም፣ የተቃዋሚ ደጋፊዎች ቁጣቸውን በአደባባባይ በመውጣት ገልጸዋል። በምርጫው ባለፈው ማክሰኞ ከተካሄደ ወዲህ በተቃዋሚዎች እና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተፈጠረ ግጭት በመዲናይቱ ናይሮቢ ከ30 የሚበልጥ ሰው መገደሉ በይፋ ተገልጿል። በተቃዋሚዎች ዘገባ መሰረት፣ በፖሊስ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ100 እንደሚበልጥ ነው የተነገረው። የሃገሪቱ ፕሬዚደንት የምርጫውን ውጤት ያልተቀበሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልጹ እና ከኃይል ተግባር እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። በሌላ በኩል ተቀናቃኛቸው ኦዲንጋ ተጭበርብሯ የሚሉትን የምርጫ ውጤት ህዝቡ በመቃወም ዛሬ በቤቱ እንዲውል እና ወደስራ ገበታው እንዳይሄድ አድማ ጠርተዋል። በኬንያ ስለቀጠለው የድህረ ምርጫ ውጥረት እንዲነግሩን ናይሮቢ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረማርያም መኮንን በስልክ ጠይቄአቸው ነበር።
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ