የኬንያ ዕቅድ እና ስደተኞች
ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008ማስታወቂያ
ስደተኞችን ከሚረዱ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ይሠራ የነበረውን የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት መዘጋቱንም መንግሥት አስታውቋል ። መንግሥት ለመዝጋት ያቀደው 328 ሺህ ስደተኞች የተጠለሉበትን የዳዳብ እንዲሁም 190 ሺህ ስደተኞች ያሉበትን የከካኩማ የስደተኞች መጠለያዎችን ነው ።ዳዳብ ከሚገኙት ስደተኞች አብዛኛዎቹ ሶማሌዎች ሲሆኑ ካኩማ ካሉት የሚያመዝኑት ደግሞ ደቡብ ሱዳናውያን ናቸው ። ኬንያ መጠለያዎቹ የአሸባሪዎች መፈልፈያ ሆነዋል ስትል ትከራከራለች ። የኬንያን እቅድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አውግዘዋል ።ስለ ኬንያ እቅድ እና ስለ ተነሳበት ተቃውሞ የናይሮቢውን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዋል።
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ