የካዉካሰሱ ግጭት ሰበብና እዉነተኛዉ ምክንያት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 27 2000ማስታወቂያ
ሐምሌ ማብቂያ የኢራቅ አፍቃኒስታንን የእልቂት-ግድያ ዜና ደፍልቆ፥ የቤጂንግ ኦሎምሊክን ድግሥ ድምቀት አፍዝዞ የመገናኛ ዘዴዎችን ገፅ-ሥርጭት ያጣበበዉ የካዉካስ ወታደራዊ ግጭት ለመቆም በርግጥ ሁለት ሳምንት አልፈጀበትም።የፖለቲካ ዲፕሎማሲዉ እሰጥ-አገባ ወታደራዊዉ ግጭት ከሚካሔድበት ጊዜ ይበልጥ ንሮ መቀጠሎ በርግጥ ግራ ነዉ።የቃላት እንኪሥላንቲያዉ፥ የዲፕሎማሲዉ ጥልፍልፍ፥ ጡንቻ ፍተሻዉ ከቲቢሊሲ፥ አብካዝ፥ ኦሲቲያ፥ ወይም ከቲቢሊሲ ሞስኮ ይልቅ የሞስኮ-ዋሽንግተን ብራሥልስ መሆኑ ደግሞ ካዉካሰስ ወትሮም ሰበብ እንጂ ምክንያቱ ሌላ መሆኑን እየመሰከረ ነዉ።የሰበብ-ምክንያቱ እንዴትነት ያፍታ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ አብራችሁኝ ቆዩ።