1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካቶሊኮቹ መሪ በዋሽግተን

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2008

ርዕሠ-ሊቀጳጳሱ ወደ ዋይት ሐዉስ ያለፉባቸዉ አዉራ መንግዶች በደጋፊያቸዉ እና በተቃዋሚያቸዉ ሠልፍኛ ተጨናንቀዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/1GbtK
የካቶሊኮቹ መሪ በዋሽግተን
ምስል Reuters/J. Ernst

[No title]

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዩናይትድ ስቴትስ የጀመሩትን ጉብኝት ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥለዋል።ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ዋይት ሐዉስ ዉስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጋር ተወያተዋል፤ ከቤተ-መንግሥቱ አካባቢ ለተሠበሰበ ሕዝብም ንግግር አድርገዋል።ርዕሠ-ሊቀጳጳሱ ወደ ዋይት ሐዉስ ያለፉባቸዉ አዉራ መንግዶች በደጋፊያቸዉ እና በተቃዋሚያቸዉ ሠልፍኛ ተጨናንቀዉ ነበር።የካቶሊካዊዉ መንፈሳዊ መሪ ትናንት ዋሽግተን ሲገቡ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦቦማ ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ተቀብለዋቸዋል።የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ