የኪርጊስታን ወቅታዊ ሁኔታ1 ሚያዝያ 2002ዓርብ፣ ሚያዝያ 1 2002በህዝባዊ አመፅ የተገለበጡት የኪርጊስታኑ ፕሬዝዳንት ኩርማንቤክ ባክየቭ ከሥልጣን የመውረድ ሀሳብ እንደሌላቸው አስታወቁ ። ሆኖም ህዝባዊው አመፅ ሲባባስ ከመዲናይቱ ከቢሽኬክ ለመውጣት የተገደዱት ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን ከያዘው ከጊዜያዊው አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል ።https://p.dw.com/p/Ms4pምስል APማስታወቂያበሌላም በኩል የኪርጊስታን የሽግግር መንግስት በአመጹ የተገደሉትን ዜጎች ለማሰብ ከዛሬ ጀምሮ የሁለት ቀናት ሀዘን አውጇል ። ፕሬዝዳንቱን ለማውረድ በተካሄደው አመፅ የተገደሉት ዜጎች የቀብር ስነ ስርዓትም ዛሬ ተካሂዷል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ