የከሰሩ ባንኮችን መንግስት የመጠቅለሉ ሂደት በጀርመን12 የካቲት 2001ሐሙስ፣ የካቲት 12 2001የጀርመን ካቢኔ ክስረት የደረሰባቸዉን የግል ባንኮች ወደመንግስት የመጠቅለል እቅድ ትናንት አጸደቀ። የዚህ ዓይነቱ ርምጃ በመጀመሪያ ተግባራዊ የሚሆነዉም ለግንባታ ብድር በሚሰጠዉና የፋይናንስ ቀዉሱን ተከትሎ ክስረት ባሽመደመደዉ ሂፖ ሪል ኤስቴት / HRE /በተሰኘዉ ተቋም ይሆናል።https://p.dw.com/p/Gxc8...HRE በቀይ መብራት ...ምስል picture alliance/dpaማስታወቂያ ቀደም ሲል ባንኩ የደረሰበትን ክስረት ያጤነዉ የጀርመን መንግስት ለድርጅቱ ከ80 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ቢሰጥም መሻሻል አላሳየም። ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲህ በጀርመን የግል ዘርፉን የመንከባከቡን ሂደት ይፃረራል በተባለዉ በዚህ ህግ ላይ ትችት የሚሰነዝሩ በርክተዋል። sl