የኦጋዴን ጉዳይ ወደICC9 የካቲት 2004ዓርብ፣ የካቲት 9 2004ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የሚገኙ የኦጋዴን ማኅበረሰብ አባላት ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኢትዮጵያ ዉስጥ በኦጋዴን አካባቢ ይፈጸማል ያሉትን የመብት ጥሰት እንዲመረምር አመለከቱ። ማኅበረሰቡ ዓለም ዓቀፉ ፍድር ቤት የተቋቋመበትን የሮም ዉል፤https://p.dw.com/p/145C1ምስል picture alliance/dpaማስታወቂያ የፈረመችዉ ደቡብ አፍሪቃም በዚህ ረገድ ሚናዋን እንድትወጣ ጠይቀዋል። ለዚህ መነሻም በመረጃነትና በአስረጅነት ጥቃት እንደተፈጸመባቸዉ የገለፁ የሶስት የአካባቢዉ ተወላጆች ጉዳይ መነሻ እንደሚሆን ነዉ ጉዳዩን የያዙት የህግ ባለሙያ የገለፁት። ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ጉዳዩን የያዙትን የህግ ሰዉ ያነጋገረችዉ ሸዋዬ ለገሠ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅራለች። ሸዋዬ ለገሠ ሂዱት መለሰ