የኦነግ ማስተባበያና የአብን መልስ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011ማስታወቂያ
በአማራ ክልል ሰሞኑን በተከሰተዉ ጥቃት ላይ እጄ የለበትም ሲል በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውየኦሮሞ ነፃነት ግንባር «ኦነግ» ገለፀ፡፡ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለዶይቼ ቬለ «DW» እንደተናገሩት «ኦነግ» በስፍራው የሚመራው የታጠቀ ሰራዊት የለዉም ይልቁንም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ የያዘና ሌሌ የታጠቀ አካል የፈጠረው ቀውስ ነው ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቁ «አብን» ኮንነዋል፡፡ ግንባሩ ይህንን ይበል እንጅ ዜጎች ለሞትና የአካል ጉዳት ብሎም ለከፍተኛ ሽብር የተዳረጉበት ይህን ድርጊት ፈጻሚው ኦነግ ነው በማለት የአካባቢው መስተዳድር አካላት ተናግረዋል፡፡ አብን በበኩሉ እንዲህ ያለው ውንጀላ በአደባባይ የተፈጸመን ወንጀል ለመደባበስ የተደረገ ስም ማጥፋት እንጅ እኛ በሰላማዊ ሁኔታ የምንታገል ነን ብሏል፡፡ የችግሩ ዋና ምንጭ በስለጣን ላይ ያለው መንግስት ህግን ማስከበር ያለመቻል ነው ብሎታል፡፡
ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ