የኦባማ ጋዜጣዊ መግለጫ
ሐሙስ፣ ኅዳር 6 2005ማስታወቂያ
የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሪፐብሊካውያን እንደሚፈልጉት ለባለሃብቶች የግብር ፋታ እንደማይሰጡ ዳግም አስታወቁ ። ኦባማ ለ 2 ተኛ የሥልጣን ዘመን ከተመረጡ በኋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለሃብታም አሜሪካውያን ያቀዱትን የግብር ጭማሪ ሃገሪቱን ከኤኮኖሚ ውድቀት ለማዳን ሲሉ ሪፐብሊካውያን መቀበል እንዳለባቸውም አሳስበዋል ። ከአጠቃላዩ ህዝብ 2 በመቶ በሚሆኑት አሜሪካውያን የግብር ጭማሪ መደረጉን ሪፐብሊካውያን ይቃወማሉ ። ኦባማ በትናንቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው በኢኮኖሚ በውጭ ግንኙነት በስደተኞችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ