1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦባማ ጉብኝት በኒውዮርክ ግራውንድ ዜሮ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 28 2003

የአልቃይዳው መሪ ኦስማ ቢን ላደን በአሜሪካ ኮማንዶዎች አቦታባድ በተሰኘች የፓኪስታን ከተማ ከተገደሉ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል። ኦባማ በመስከረም 11 ለተገደሉት የመታሰቢያ አበባ አኖሩ።

https://p.dw.com/p/RMQL
የኦባማ ጉብኝት በኒውዮርክ ግራውንድ ዜሮምስል A

እ.ኤ.አ መስከረም 11 2001 ለደረሰውና ከ3ሺህ በላይ ሰዎች ላለቁበት የሽብር ጥቃት ተጠያቂ የሆኑት ቢን ላደን መገደላቸዉ አሜሪካ ጥቃትዋን መቼም እንደማትረሳ ያሳያል ብለዋል- ፕሬዝዳንት ኦባማ። ኦባማ ይህን የተናገሩት የቢን ላደንን መገደል ለማብሰርና በኒውዮርኩ ጥቃት የተገደሉትን ለማሰብ በተዘጋጀው ስነ ስርዓት ላይ ነው። ፕሬዝዳንት ኦባማ ኒውዮርክ አቅንተው የመታሰቢያ የአበባ ጉንጉንም አኑረዋል።

አበበ ፈለቀ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሀመድ