የኦባማ የኩባ ጉብኝት
ሰኞ፣ መጋቢት 12 2008ማስታወቂያ
ፕሬዝደንት ኦባማ ቤተሰቦቻቸዉን አስከትለዉ ትናንት ኩባ የገቡት በአሜሪካን እና ኩባ መካከል ከ50 ዓመታት በላይ የተቋረጠዉ ግንኙነት ዓለምን ባስገረመ መንገድ ከአንድ ዓመት በፊት እንደ አዲስ ከተሻሻለ በኋላ ነዉ። ባራክ ኦባማ ከ88ዓመታት ወዲህ ኩባን የጎበኙ የመጀመሪያዉ አሜሪካዊ ፕሬዝደንትም ተብለዋል። የኦባማ ጉብኝት በሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ላይ ምን ያመጣል ብሎ መገመት ይቻል ይሆን? የዋሽንግተን ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴን በዚህ ጉዳይ ላይ በስልክ በአጭሩ አነጋግሬዋለሁ፤
ናትናኤል ወልዴ
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ