የኦባማ ፤ የእስካሁን የሥራ እቅዶችና ክንውኖች
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 29 2004ማስታወቂያ
የዩናይትድ እስቴትስ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ዛሬ ማምሻውን በሚከፈተው ዐቢይ ጉባዔው፣ በጥቅምት ወር ማለቂያ ገደማ በሚካሄደው ምርጫ ፣ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፣ዳግመኛ ማሸነፍ ከቻሉ ፤ በቀጣይ ዐራት ዓመታት የሚያከናውኗቸውን መርኀ ግብሮች በያፋ እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል።እቅዶቹ የተዘረዘሩበት ሰነድ መሪ ቃል « አሜሪካን ወደፊት ማራመድ!» የሚል ነው።የወደፊቱ ትልም ከመገለጡ በፊት ፤ ባራክ ኦባማ፣ ባለፉት 4 ዓመታት ገደማ አስቀድመው የወጠኗቸው ዐበይት የሥራ እቅዶች እስከምን ድረስ ተከናውነዋል? የገቡትን ቃል እስከምን አክብረዋል? የዋሽንግተን ዲ ሲ ው ዘጋቢአችን አበበ ፈለቀ፤ የኦባማን የ 4 ዓመት የሥራ እቅድና ክንውን የዳሰሰበትን የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።
አበበ ፈለቀ
ተክሌ የኋላ