የኦባማ ዓመታዊ የመርህ ንግግር
ረቡዕ፣ ጥር 21 2006ማስታወቂያ
ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የሪፐብሊካኖች ተቃውሞ እቅዳቸውን ለማሳካት እንቅፋት የሆነባቸው ኦባማ ትናንት ማታ ባሰሙት ዓመታዊ የመርህ ንግግራቸው የአሜሪካን ምክር ቤትን ሥልጣን ሳይጠበቁ ሥልጣናቸውን በመጠቀም እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ገልፀዋል ። በንግግራቸው በአሜሪካን ህዝብ መካከል የሚታየውን ሰፋ የገቢ ልዩነት ለማስተካከልና የሠራተኞችንም ዝቅተኛ የክፍያ መጠን ከፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ። ይበልጡን በሃገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ ባተኮረው የአንድ ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ንግግራቸው ኦባማ የውጭ መርህቸውንም በአጭሩ አሳውቀዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ