የኦሮሞ ጥናት ማህበር ዓመታዊ ስብሰባ በዋሽንግተን27 ሐምሌ 2007ሰኞ፣ ሐምሌ 27 2007ኦሮሞ ጥናት ማህበር ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በዋሽንግተን ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ ስብሰባውን አካሄደ። ከተያዩ ሃገራት የሄዱ የኦሮሞ እና ኦሮሞ ያልሆኑ ምሁራን በዚሁ ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን አቅርበዋል። ጥናቶቹ በኦሮሞ ህዝብ ባህል፣ አኗኗር፣ እንዲሁም፣https://p.dw.com/p/1G95Vምስል dpa - Bildfunkማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio በማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ነበሩ። በስብሰባው ከተገኙት በርካታ እንግዶች መካከል በኢትዮጵያ ከጥቂት ጊዜ በፊት ከእስራት የተለቀቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር አቶ በቀለ ገርባ እና እውቁ የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጆን ማርካኪስ ዋነኞቹ ነበሩ። መክብብ ሸዋ አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ