የኦሮሞ ማሕበረሰብ ተቃውሞ በለንደን
ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2008ማስታወቂያ
ከገለልተኛ ወገን ማጣራት ባይቻልም የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሟቾች ቁጥር ከለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑን በማህበራዊ ድረ-ገጾች የተሰራጩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። በብሪታኒያ ዋና ከተማ ለንደን ዛሬ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። በለንደን ዛሬ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ የዶይቼ ቬለ ወኪል ድልነሳው ጌታነህ ተመልክቶታል።
ድልነሳው ጌታነህ
እሸቴ በቀለ
ሒሩት መለሰ