1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ማህበረሰብ ገለፃ ለአሜሪካን እንደራሴዎች

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2008

የማህበረሰቡ አባላት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሰጠው የልማትና የጦር መሣሪያ ድጋፍ በኦሮምያ ክልል የተከሰተውን ተቃውሞ በኃይል ለመቀልበስ ውሏል ሲሉ ይከሳሉ ።

https://p.dw.com/p/1IZ9d
Capitol Hill in Washington
ምስል Illuscope

[No title]

በአሜሪካን ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ከጥቂት ወራት በፊት በኦሮምያ ክልል ስለተካሄደው ህዝባዊ አመፅና መንግሥት ስለወሰዳቸው እርምጃዎች ለአሜሪካን የህዝብ እንደራሴዎች ገለፃ አደረጉ ። እነዚሁ ከ30 የተለያዩ የአሜሪካን ክፍለ ግዛቶች የተሰባሰቡት የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላትና የመብት ተሟጋቾች ማብራሪያውን የሰጡት ለየሚገኙባቸው ክፍለ ግዛቶች ና ዋሽንግተን ዲሲ ላሉ የህዝብ እንደራሴዎች ነው ። የማህበረሰቡ አባላት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሰጠው የልማትና የጦር መሣሪያ ድጋፍ በኦሮምያ ክልል የተከሰተውን ተቃውሞ በኃይል ለመቀልበስ ውሏል ሲሉ ይከሳሉ ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።
ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ